ዳንኤል 5:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ እንዳለና ብልኀት፥ ዕውቀትና ጥበብ የተሰጠህ መሆኑን ሰምቼአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአማልክት መንፈስ በውስጥህ እንዳለ፣ ዕውቀት፣ ማስተዋልና ልዩ ጥበብ እንዳለህ ሰምቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአማልክት መንፈስ እንዳለብህ፥ እውቀትና ማስተዋልም መልካምም ጥበብ እንደ ተገኘብህ ስለ አንተ ሰምቻለሁ። |
ከዚህ በኋላ በአምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የሚጠራው ዳንኤል ገባ፤ ይህ ሰው የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያደረበት ነው፤ እንዲህም ስል ሕልሜን ነገርኩት፤
በዚያኑ ጊዜ ዳንኤል በንጉሡ ፊት ቀረበ፤ ንጉሡም እንዲህ አለው፦ “አባቴ ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ካመጣቸው ከይሁዳ ስደተኞች መካከል አንዱ የሆንክ ዳንኤል አንተ ነህን?
እነሆ፥ ጠቢባን አማካሪዎቼና አስማተኞች ሁሉ ይህን ጽሕፈት አንብበው እንዲተረጒሙልኝ ተጠርተው ወደ እኔ መጥተው ነበር፤ ነገር ግን ተርጒመው ሊያስረዱኝ አልቻሉም፤
ዳንኤል ባለው ልዩ የሥራ ችሎታ ከሌሎቹ አገረ ገዢዎችና ባለ ሥልጣኖች በልጦ መገኘቱን በተግባር አስመሰከረ፤ ስለዚህ ንጉሡ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሊሾመው አሰበ።