ቈላስይስ 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማንኛውም አጋጣሚ ጊዜ እየተጠቀማችሁ በማያምኑት ሰዎች ዘንድ በጥበብ ኑሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውጭ ካሉት ሰዎች ጋራ ባላችሁ ግንኙነት በጥበብ ተመላለሱ፤ በተገኘውም ዕድል ሁሉ ተጠቀሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘመኑን እየዋጃችሁ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘመኑን እየዋጃችሁ ከሃይማኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማስተዋል ሂዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። |
ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ የወሰንኩትን ጥብቅ ውሳኔ ስላወቃችሁ የእናንተ ዕቅድ ነገሩን ለማዘግየት መሆኑን ተረድቼአለሁ፤
እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጪ ላሉት ግን ሁሉ ነገር በምሳሌ ይነገራቸዋል።
ለወንጌል ቃል ታዛዦች መሆናችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ ስለ ታወቀ ደስ ያለኝ ቢሆንም፥ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር ግን የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።
ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ ታዛዥ፥ ምሕረት አድራጊ፥ ጥሩ ፍሬ የሞላበት፥ አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።
እንዲሁም እናንተ ሚስቶች! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዐይነት አንዳንዶች በእግዚአብሔር ቃል የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃሉ ትምህርት በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል።