ሐዋርያት ሥራ 26:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተለየም አንተ የአይሁድን ሥርዓትና ክርክር ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ፤ ስለዚህ በትዕግሥት እንድታዳምጠኝ እለምንሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም አንተ በተለይ የአይሁድን ልማድና ክርክር ሁሉ በሚገባ ስለምታውቅ ነው፤ ስለዚህ በትዕግሥት እንድታደምጠኝ እለምንሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአይሁድን ጠባያቸውንና ክርክራቸውን አጥብቀህ ታውቃለህና ታግሠህ ታደምጠኝ ዘንድ እለምንሃለሁ። |
አንተ በአሕዛብ መካከል የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ ‘ልጆቻችሁን አትግረዙ ወይም ሥርዓቶችን አትፈጽሙ’ እያልክ በማስተማር የሙሴን ሕግ እንዲሽሩ ታደርጋለህ እየተባለ የሚወራውን ሰምተዋል።
አገረ ገዥው ፊልክስ በእጁ ጠቅሶ ጳውሎስ እንዲናገር ፈቀደለት፤ ጳውሎስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለብዙ ዓመቶች የዚህ አገር ገዢ መሆንክን ስለማውቅ ለቀረበብኝ ክስ መከላከያዬን በአንተ ፊት ሳቀርብ በጣም ደስ እያለኝ ነው፤
ይሁን እንጂ ስለ እርሱ ለጌታዬ የምጽፈው የተረጋገጠ ነገር የለኝም፤ ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈው ነገር እንዳገኝ ብዬ በፊታችሁ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! በፊትህ አቅርቤዋለሁ።
ወደዚህ ተስፋ ለመድረስ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን እግዚአብሔርን ሌት ተቀን እያመለኩ ይጠባበቁ ነበር፤ ንጉሥ ሆይ! እኔም በአይሁድ የተከሰስኩበት በዚህ ተስፋ ምክንያት ነው።
ከሦስት ቀን በኋላ ጳውሎስ በሮም የሚኖሩትን የአይሁድን ታላላቅ ሰዎች አስጠራ፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ በእስራኤል ሕዝብ ላይና በአባቶች ሥርዓት ላይ ያደረግኹት ምንም በደል የለም፤ ይሁን እንጂ በኢየሩሳሌም ታስሬ ለሮማውያን ተላልፌ ተሰጠሁ።
ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝና ምሥጢርንም ሁሉ ብረዳ፥ ዕውቀትም ሁሉ ቢኖረኝ፥ ተራራን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያፈልስ እምነትም ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
ይልቅስ ንጉሥ በሚሆንበት ጊዜ እነዚህ በሌዋውያን ካህናት ተጠብቀው የሚኖሩት የእግዚአብሔር ሕግጋት የተጻፉበትን መጽሐፍ አንድ ቅጅ እንዲኖረው ያድርግ።