ሐዋርያት ሥራ 16:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጳውሎስ ይህን ራእይ ካየ በኋላ ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ፈለግን፤ ይህም የሆነው ለመቄዶንያ ሰዎችም ወንጌልን እንድናስተምር ጌታ እንደ ጠራን ስለ ተረዳን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስ ይህን ራእይ ካየ በኋላ፣ እግዚአብሔር ወንጌልን እንድንሰብክላቸው ጠርቶናል ብለን በመወሰን ወዲያው ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ፈለግን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፤ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራእዩንም ባየ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ልንሄድ ወደድን፤ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር የሚጠራን መስሎናልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና። |
ንጉሥ ሆይ! በመንገድ ሳለሁ ልክ እኩለ ቀን ሲሆን ከፀሐይ ብርሃን የሚበልጥ ብርሃን አየሁ፤ ይህም ብርሃን በእኔና ከእኔ ጋር በሚጓዙት ሰዎች ዙሪያ ከሰማይ አበራ።
ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው።
በዚያን ጊዜ በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታ በራእይ “ሐናንያ!” ብሎ ጠራው፤ እርሱም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” አለ።