ኢዮአብ አበኔርን ከማሳደድ በተመለሰ ጊዜ ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ በዚህ ጊዜ ከዳዊት ሰዎች መካከል ከዐሣሔል ሌላ ዐሥራ ዘጠኝ ሰዎች መጒደላቸው ታወቀ።
2 ሳሙኤል 2:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔርና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ በመጓዝ በዓራባ ሸለቆ በኩል ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግረው በመጓዝ ቢትሮንን ሁሉ ዓልፈው ወደ ማኅናይም መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ዓረባን ዐልፈው ሄዱ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን በመሻገር ቢትሮንን ሁሉ ዐልፈው ወደ መሃናይም መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ዓራባን አልፈው ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም በመሻገር ቢትሮንን ሁሉ ዐልፈው ወደ ማሕናይም መጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ወደ ምዕራብ ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፤ ያን ቀጥተኛ መንገድ ካለፉ በኋላም ወደ ሰፈር መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ዓረባ እያለፉ ሄዱ፥ ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፥ ቢትሮንንም ሁሉ ካለፉ በኋላ ወደ መሃናይም መጡ። |
ኢዮአብ አበኔርን ከማሳደድ በተመለሰ ጊዜ ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ በዚህ ጊዜ ከዳዊት ሰዎች መካከል ከዐሣሔል ሌላ ዐሥራ ዘጠኝ ሰዎች መጒደላቸው ታወቀ።
ከገቡም በኋላ ወደ ኢያቡስቴ መኝታ ክፍል ዘለቁ፤ እርሱም በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ወግተው ገደሉት፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱ፤ ሌሊቱንም ሁሉ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ በኩል አልፈው ሄዱ፤
የሌሊቱ ጨለማ እስከሚወገድ፤ የማለዳው ነፋስ እስከሚነፍስ፤ ውዴ ሆይ! እንደ ዋልያ ወይም እንደ አጋዘን ግልገል በገደላማ ተራራዎች ላይ እየሮጥክ ተመለስ።