መልካም ነገር አድርገህ ቢሆን ኖሮ ተቀባይነት አይኖርህም ነበርን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በበርህ ላይ ያደባል፤ በቊጥጥሩ ሥር ሊያደርግህም ይፈልጋል፤ ሆኖም አንተ ልታሸንፈው ይገባል።”
2 ሳሙኤል 11:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳዊት “ሒታዊውን ኦርዮን ወደ እኔ ላከው” ሲል ወደ ኢዮአብ መልእክት ሰደደ፤ ስለዚህም ኢዮአብ ኦርዮን ወደ ዳዊት ላከው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ዳዊት ለኢዮአብ፣ “ኬጢያዊውን ኦርዮን ወደ እኔ ስደደው” ሲል ላከበት፤ ኢዮአብም ወደ ዳዊት ላከው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ዳዊት ለኢዮአብ፥ “ሒታዊውን ኦርዮንን ወደ እኔ ስደደው” ሲል ላከበት፤ ኢዮአብም ኦርዮንን ወደ ዳዊት ላከው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ኢዮአብ፦ ኬጤያዊውን ኦርዮን ወዲህ ላከው ብሎ ላከ። ኢዮአብም ኦርዮን ወደ ዳዊት ላከው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ ኢዮአብ፦ ኬጢያዊውን አርዮን ስደድልኝ ብሎ ላከ። ኢዮአብም ኦርዮን ወደ ዳዊት ሰደደው። |
መልካም ነገር አድርገህ ቢሆን ኖሮ ተቀባይነት አይኖርህም ነበርን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በበርህ ላይ ያደባል፤ በቊጥጥሩ ሥር ሊያደርግህም ይፈልጋል፤ ሆኖም አንተ ልታሸንፈው ይገባል።”
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ሳኦልም “በእርግጥ በደል ሠርቼአለሁ፤ ይሁን እንጂ ሌላው ቢቀር በሕዝቤ መሪዎችና በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር አብረህ ሂድ” ሲል ለመነው።