La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 22:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የመሹላም የልጅ ልጅ፥ የአጻልያ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ሳፋንን ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዘመነ መንግሥቱ በዐሥራ ስምንተኛውም ዓመት ኢዮስያስ የሜሶላምን የልጅ ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ጸሓፊውን ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላከው፤ እንዲህም አለው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የመሹላም የልጅ ልጅ፥ የአጻልያ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ሳፋንን ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በን​ጉ​ሡም በኢ​ዮ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ንጉሡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ጸሓፊ የሜ​ሱ​ላ​ምን ልጅ የኤ​ሴ​ል​ዩን ልጅ ሳፋ​ንን እን​ዲህ ሲል ላከው፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በንጉሡም በኢዮስያስ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር ንጉሡ ጸሐፊውን የሜሶላምን ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤት ላከው፤ እንዲህም አለው

Ver Capítulo



2 ነገሥት 22:3
7 Referencias Cruzadas  

ሣጥኑም በሚሞላበት ጊዜ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ እየመጡ ብሩን በመቊጠር በከረጢት እያሰሩ ያኖሩት ነበር።


ይሁን እንጂ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ተከበረ።


ይህም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ የመጣው የዐሞን ልጅ ኢዮስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ነው።


ሕዝቡም ለማዳመጥ በሚችልበት ሁኔታ ባሮክ እኔ የነገርኩትን በብራና ጽፎት የነበረውን ቃል ሁሉ አነበበላቸው። በቤተ መቅደስ ውስጥ ይህን ያደረገው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል በኩል ዘልቆ ነበር፤ ክፍሉም የሚገኘው ወደ ቤተ መቅደስ ከሚያስገባው አዲስ የቅጽር በር አጠገብ በላይኛው አደባባይ በኩል አለፍ ብሎ ነበር።


የሳፋን የልጅ ልጅ የነበረው የገማርያ ልጅ ሚክያስ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ሁሉ ባሮክ ከብራናው ሲያነብ ሰማ።


እርሱም በቤተ መንግሥት ወደሚገኘው ባለሥልጣኖች ወደሚገኙበት ወደ ጸሐፊው ክፍል ሄደ፤ ጸሐፊው ኤሊሻማዕ፥ የሸማዕያ ልጅ ደላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ ሌሎችም ባለ ሥልጣኖች እዚያ ተቀምጠው ነበር።