ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።
1 ሳሙኤል 18:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የለበሰውንም ካባ አውልቆ ለዳዊት ሰጠው፤ እንዲሁም የጦር ልብሱን፥ ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ጭምር ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፣ በተጨማሪም ሰይፉን፣ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፥ በተጨማሪም ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም የለበሰውን ካባ አውልቆ እርሱንና ልብሱን፥ ሰይፉንም፥ ቀስቱንም፥ ዝናሩንም ለዳዊት ሸለመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም የለበሰውን ካባ አውልቆ እርሱንና ልብሱን ሰይፉንም ቀስቱንም መታጠቂያውንም ለዳዊት ሸለመው። |
ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
አባቱ ግን አገልጋዮቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ ‘ቶሎ ብላችሁ ከሁሉ የበለጠውን ልብስ አምጡና አልብሱት! በጣቱ ቀለበት፥ በእግሩም ጫማ አድርጉለት!
ሳኦል በትእዛዝ በሚያዘምትበት ቦታ ሁሉ የዳዊት ተልእኮ የተሳካ ሆነ፤ ስለዚህም ሳኦል በጦር ሠራዊቱ ውስጥ የመኰንንነት ማዕርግ እንዲኖረው አደረገ፤ ይህም የሳኦልን የጦር መኰንኖችና ወታደሮችን ሁሉ አስደሰተ።