በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።
1 ነገሥት 15:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሳ በኰረብቶች ላይ የሚገኙ የአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎችን በሙሉ ባያስወግድም እንኳ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ኖረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሳ የማምለኪያ ኰረብቶችን ፈጽሞ ባያስወግድም እንኳ በዘመኑ ሁሉ፣ ልቡ ለእግዚአብሔር ፍጹም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳ በኰረብቶች ላይ የሚገኙ የአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎችን በሙሉ ባያስወግድም እንኳ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ ለጌታ ታማኝ ሆኖ ኖረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በኮረብቶች ላይ ያሉትን መስገጃዎች አላራቀም፤ የአሳ ልብ ግን በዘመኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በኮረብቶች ላይ ያሉትን መስገጃዎች አላራቀም፤ የአሳ ልብ ግን በዘመኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ነበረ። |
በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።
አቢያም፥ እንደ ታላቁ አያቱ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ታማኝ ሆኖ በመገኘት ፈንታ፥ አባቱ ሮብዓም ይፈጽመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራቱን ቀጠለ።
ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ሠራ፤ ይሁን እንጂ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን አልደመሰሰም ነበር፤ ስለዚህም ሕዝቡ በእነዚያ ቦታዎች መሥዋዕት ማቅረብና ዕጣን የማጠን ተግባሩን አልተወም ነበር፤
ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።
ይሁን እንጂ በየኰረብታዎች ላይ የሚገኙት የአሕዛብ ማምለኪያዎች ስላልተደመሰሱ፥ ሕዝቡ በዚያ ዕጣን እያጠኑ መሥዋዕት ማቅረባቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር።
ይኸውም በየኰረብታዎች ላይ የተሠሩትን የአሕዛብ ማምለኪያዎችን አላፈረሰም፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ በየኮረብታዎቹ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጠኑን እንደ ቀጠለ ነበር።
ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብን የማምለኪያ ቦታዎች አልደመሰሰም፤ ስለዚህም ሕዝቡ በየኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤
ባዕዳን መሠዊያዎችንና በኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን አስወገደ፤ ለማምለኪያ የተሠሩ የድንጋይ ዐምዶችን ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎችን አንከታክቶ ጣለ፤
እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”
አሜስያስ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ያደርግ ነበር፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ የሚያደርገውን ነገር በሙሉ ልብ አያደርግም ነበር፤