ከግብጽ ለሚገዛው ለያንዳንዱ ሠረገላ ስድስት መቶ ጥሬ ብር ለያንዳንዱ ፈረስ አንድ መቶ ኀምሳ ጥሬ ብር ይከፍሉ ነበር። እነርሱም መልሰው ለሒታውያንና ለሶርያ ነገሥታት ይሸጡላቸው ነበር።
1 ነገሥት 10:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠረገሎችን ከግብጽ አገር በማስመጣት፥ ለእያንዳንዱ ሠረገላ ስድስት መቶ ጥሬ ብር፥ ለእያንዳንዱም ፈረስ አንድ መቶ ኀምሳ ጥሬ ብር ይከፍሉ ነበር፤ ከዚያም እነርሱ ለሒታውያንና ለሶርያ ነገሥታት ይሸጡላቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ ያስመጧቸውም አንዱን ሠረገላ በስድስት መቶ ሰቅል ብር፣ አንዱን ፈረስ በአንድ መቶ ዐምሳ ሰቅል ብር ገዝተው ነው። እነዚህንም ደግሞ ለኬጢያውያንና ለሶርያውያን ነገሥታት ሁሉ ይሸጡላቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠረገሎችን ከግብጽ አገር በማስመጣት፥ ለእያንዳንዱ ሠረገላ ስድስት መቶ ጥሬ ብር፥ ለእያንዳንዱም ፈረስ አንድ መቶ ኀምሳ ጥሬ ብር ይከፍሉ ነበር፤ ከዚያም እነርሱ ለሒታውያንና ለሶርያ ነገሥታት ይሸጡላቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱም ሰረገላ በስድስት መቶ፥ አንዱም ፈረስ በመቶ ኀምሳ ብር ከግብፅ ይወጣ ነበር። እንዲሁም ለኬጤዎናውያን ነገሥታትና ለሶርያ ነገሥታት ሁሉ በባሕሩ በኩል ያወጡላቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱም ሠረገላ በስድስት መቶ፥ አንዱም ፈረስ በመቶ አምሳ ብር ከግብጽ ይወጣ ነበር። እንዲሁም ሒታውያንና ለሶርያ ነገሥታት ሁሉ በእጃቸው ያወጡላቸው ነበር። |
ከግብጽ ለሚገዛው ለያንዳንዱ ሠረገላ ስድስት መቶ ጥሬ ብር ለያንዳንዱ ፈረስ አንድ መቶ ኀምሳ ጥሬ ብር ይከፍሉ ነበር። እነርሱም መልሰው ለሒታውያንና ለሶርያ ነገሥታት ይሸጡላቸው ነበር።
ድንበራችሁ በስተደቡብ ካለው ምድረ በዳ ተነሥቶ በስተሰሜን እስከሚገኙት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች ድረስ፥ በስተምሥራቅ ከትልቁ ወንዝ ከኤፍራጥስ፥ በመነሣት የሒታውያንን ምድር ሁሉ ጨምሮ በምዕራብ በኩል እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሆናል።
ከዚህም በኋላ ዳዊት ሒታዊውን አቤሜሌክንና ከጸሩያ ልጆች የኢዮአብን ወንድም አቢሳን “ከእናንተ ከሁለታችሁ ከእኔ ጋር አብሮ ወደ ሳኦል ሰፈር የሚሄድ ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሻይም “እኔ እሄዳለሁ” ሲል መለሰ።