La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 7:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ማንም ሰው ከተገረዘ በኋላ የተጠራ ከሆነ እንዳልተገረዘ ለመሆን አያስብ፤ ሳይገረዝ የተጠራ ከሆነም መገረዝን አይፈልግ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድ ሰው ተገርዞ ሳለ ቢጠራ፣ እንዳልተገረዘ ሰው አይሁን፤ ሳይገረዝም ተጠርቶ ከሆነ አይገረዝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደሆነ፥ መገረዝን አይፈልግ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ተገ​ዝሮ ሳለ የተ​ጠራ ቢኖር አለ​መ​ገ​ዘ​ርን አይ​መኝ፤ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም ቢጠራ ከዚያ ወዲያ አይ​ገ​ዘር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 7:18
8 Referencias Cruzadas  

“ስለዚህ የእኔ አሳብ ወደ እግዚአብሔር የሚመለሱትን አሕዛብ እንዳናስቸግራቸው ነው።


ከእኛ መካከል አንዳንድ ሰዎች እኛ ሳናዛቸው ወደ እናንተ መጥተው በነገሩአችሁ ቃል እንዳስቸገሩአችሁና ግራ እንዳጋቡአችሁ ሰምተናል፤


ከእነዚህ ከሚከተሉት አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር ሌላ ከባድ ሸክም እንዳንጭንባችሁ መንፈስ ቅዱስና እኛ መልካም ሆኖ አግኝተነዋል፤


ነገር ግን ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ አማኞች ተነሡና “አሕዛብ እንዲገረዙና የኦሪትን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ ይገባል” አሉ።


አንተ በአሕዛብ መካከል የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ ‘ልጆቻችሁን አትግረዙ ወይም ሥርዓቶችን አትፈጽሙ’ እያልክ በማስተማር የሙሴን ሕግ እንዲሽሩ ታደርጋለህ እየተባለ የሚወራውን ሰምተዋል።


በዚህ ሁኔታ በግሪካዊና በአይሁዳዊ፥ በተገረዘና ባልተገረዘ፥ በሠለጠነ አረመኔና ባልሠለጠነ አረመኔ፥ ነጻነት በሌለውና ነጻነት ባለው ሰው መካከል ልዩነት የለም፤ ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው።