ለዚህ ድርብ ወንጀል ግን ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፥ ጣኦቶችን በማምለክ እግዚአብሔርን አዋርደዋልና፤ ቅድስናውንም በመናቅ በተንኮል የሐሰት መሐላ አድርገዋልና።
እውነተኛ ፍርድ በአንድነት ያገኛቸዋል፥ ጣዖቱን በተመለከቱ ጊዜ በእግዚአብሔር ክፉ ነገርን ዐስበዋልና፥ የፈጣሪን እውነት አቃልለው በግፍና በሐሰት ምለውበታልና።