ያለ ዕድሜው በተቀጨ ልጅ ኀዘን የትናንቱን ሬሣ ዛሬ ያመለከዋል፤ ምሥጢሩንና ሥርዓቱንም ለወገኖቹ ያስተላልፋል።
ልጁ ሕፃን ሳለ ፈጥኖ በሞት ስለ ተነጠቀ አባቱ ላንድ ልጁ ይጨነቅና ያለቅስ ነበርና፥ ቀድሞ ለሞተው ልጁ ምስል ሠራለት፥ ዛሬ ግን እንደ አምላክ አድርገው አከበሩት። ለኀጢአት የተገዙ ሰዎችም በስውር በዓል አደረጉለት፥ የምሥጢር መሥዋዕትንም ሠዉለት።