ማሕልየ መሓልይ 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገነቱ የምትቀመጪ ሆይ፥ ባልንጀሮች የአንቺን ድምፅ ይሰማሉ፥ ድምፅሽን አሰሚኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ በአትክልቱ ቦታ የምትኖሪ ሆይ፤ ባልንጀሮቼ ድምፅሽን ይሰማሉ፤ እስኪ እኔም ልስማው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ የእኔ ሙሽራ ሆይ! በአትክልት ቦታ ሆነሽ ጓደኞቼ ድምፅሽን ለመስማት ይፈልጋሉ፤ እስቲ ለእኔ ድምፅሽን አሰሚኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአትክልቱ ቦታ ሲኖር ሌሎች አዩት፥ ቃልህን አሰማኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገነቱ የምትቀመጪ ሆይ፥ ባልንጀሮች የአንቺን ቃል ያደምጣሉ፥ ቃልሽን አሰሚኝ። |
ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመስጋለህ? ስለ ምንስ ከባልንጀሮችህ መንጎች በኋላ እቅበዘበዛለሁ?
እርሱም፥ “በይ ሂጂ” ብሎ ለሁለት ወር አሰናበታት፤ እርሷም ከእንግዲህ ባል ስለማታገባ ከልጃገረድ ጓደኞቿ ጋር ወደ ተራሮች ሄደው አለቀሱ።