ማሕልየ መሓልይ 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውዴ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እንውጣ በመንደሮችም እንደር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውዴ ሆይ፤ ና ወደ ገጠር እንሂድ፤ ወደ መንደርም ገብተን እንደር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውዴ ሆይ! ና፤ ከከተማ ወጥተን ወደ ገጠር እንሂድ፤ ሌሊቱን በዚያ እናሳልፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ የልጅ ወንድሜ ነኝ፥ የእርሱም መመለሻው ወደ እኔ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው። |
ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን፥ ንጉሥ ወደ ቤቱ አገባኝ፥ በአንተ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፥ በቅንነት ይወድዱሃል።
ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።