ማሕልየ መሓልይ 5:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፉ ራሱ ጣፋጭ ነው፤ ሁለንተናውም ያማረ ነው። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ ውዴ ይህ ነው፤ ባልንጀራዬም እርሱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አፉ እንደ ማር. የጣፈጠ ነው፤ ሁለንተናውም የደስ ደስ አለው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት እንግዲህ ውዴና ወዳጄ ይህን የመሰለ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕሮሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለንተናውም የተወደደ ነው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ልጅ ወንድሜ ይህ ነው፥ ወዳጄም ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው። |
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳ ጌታ እንደሚወድዳቸው እንዲሁ አንተም ዳግመኛ ሂድ፥ በውሽማዋ የምትወደደውን አመንዝራይትን ሴት ውደድ።”
ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ እኔ አልኖርም፤ አሁን በሥጋ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ በማመን የምኖረው ነው።
አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ለማወቅ ስል ሁሉ ነገር ጉዳት እንደሆነ አድርጌ እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ነገሮች በማጣት ተጐዳሁ፤ እነርሱንም እንደ ጉድፍ አድርጌ ቈጠርኋቸው፤ በዚህም ክርስቶስን እንዳገኝ፥
አመንዝሮች ሆይ! ከዓለም ጋር ወዳጅ መሆን የእግዚአብሔር ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።