ጠላት የሆነውን ሕዝብ ወጋ፥ በቁልቁለቱም ላይ ደመሰሳቸው፥ የእርሱን ጀግንነት በጌታ ስም እንደሚዋጋ አሳያቸው።
በተጣሏቸው በአሕዛብም ላይ አዘነበባቸው፤ የተዋጓቸውንም በገደል ውስጥ አጠፏቸው፤ ሕዝቡ ኀይሉን ያውቁ ዘንድ የሚዋጋላቸው እግዚአብሔር ነውና፤ ኀይሉን አከታትሎ ከእነርሱ ጋር አደረገላቸው።