በቀሚሱ ዙሪያ የሚደረግ የሮማን መርገፍ፥ እርሱ በተራመደ ቍጥር የሚያቃጭሉ፥ ቤተ መቅደሱን በድምፃቸው የሚሞሉ፥ የሕዝቦች ልጆች መታሰቢያ የሆኑ፥ የወርቅ ደውሎችንም ሰጠው።
በዙሪያውም ብዙ ሮማንና የወርቅ ጸናጽል አለ፤ በእግሩም በረገጠ ጊዜ የመርገፉ ድምፅ በቤተ መቅደስ ይሰማ ዘንድ ይጮህ ነበር፤ ይህም ለሕዝቡና ለልጆቻቸው መታሰቢያ ሆነ።