በወርቅ የተለበጡ ጠቢብ የሠራቸው፥ እንደ ማኀተም የተቀረጹ የክብሩ ደንጊያዎች፥ የእስራኤልን ነገዶች ቍጥር በውስጣቸው የያዙ መታሰቢያዎች፥
የነጭ ሐር የሚሆን ፈትሉ እጥፍ የሆነ፥ ዕንቍም ያለበት፥ የማኅተምም ቅርጽ ያለበት ልብስን በልብስ ላይ አለበሰው፤ እጀ ጠባቡም በወርቅ የተሠራ ነው፤ በየወገናቸው መታሰቢያ ሊሆን በዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ልጆች ቍጥር ልክ የተጻፈ ነው።