La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 7:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኃጢአት ግን በትእዛዝ አማካኝነት አጋጣሚን በመውሰድ ሁሉንም ዓይነት ምኞትን አስነሣ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ የሞተ ነውና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኀጢአት ግን ትእዛዙ ባስገኘው ዕድል ተጠቅሞ በእኔ ውስጥ ማንኛውንም ዐይነት ዐጕል ምኞት አስነሣ፤ ኀጢአት ያለ ሕግ ምዉት ነውና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኃጢአት ከሕግ በመጣው ትእዛዝ ዕድል አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በኔ ውስጥ እንዲቀሰቀስ አደረገ። ሕግ ከሌለ ግን ኃጢአት የሞተ ነገር ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያችም ትእ​ዛዝ ለኀ​ጢ​አት ምክ​ን​ያት ሆነ​ቻት፤ ምኞ​ት​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ች​ብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳት​ሠራ ኀጢ​አት ሙት ነበ​ረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና።

Ver Capítulo



ሮሜ 7:8
12 Referencias Cruzadas  

መስገብገብ፥ ክፋት፥ ማታለል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስም ማጥፋት፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸው።


እኔ መጥቼ ባልነገራቸው ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀጢአታቸው ሰበብ የላቸውም።


ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተዋል፤ ጠልተውማል።


ምክንያቱም በሕግ ሥራ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና።


ሕጉ መቅሠፍትን ያስከትላልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።


በደል እንዲበዛ ሕግ ገባ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ጸጋ ይበልጥ በዛ፤


ኃጢአት በትእዛዝ በኩል አጋጣሚ አግኝቶ አታልሎኛልና፥ በእርሱም ገደለኝ።


እንግዲህ መልካም የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? በጭራሽ! ነገር ግን ኃጢአት ኃጢአትነቱ እንዲታይ፥ መልካም በሆነው ነገር ሞትን ይሠራብኝ ነበር። ይኸውም ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት ያለ ልክ ኃጢአት እንዲሆን ነው።


እንግዲህ አሁን ይህን የማደርገው እኔ ሳልሆን፥ በእኔ ውስጥ የሚያድረው ኃጢአት ነው።


እኔም ድሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ።


የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው፤ የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው።