ሮሜ 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንደምትበዙ በማመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስስላችሁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስፋችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እያደገ እንዲሄድ የተስፋ አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተስፋ አምላክ እግዚአብሔርም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በተስፋ ያበዛችሁ ዘንድ በእምነት ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይፈጽምላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ። |
አንተ የእስራኤል ተስፋ ሆይ! በመከራም ጊዜ የምታድነው፥ በምድሪቱ እንደ እንግዳ፥ ሌሊቱን ለማሳለፍ ወደ ማደርያ ዘወር እንደሚል መንገደኛ ለምን ትሆናለህ?
ጌታም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ያሰማል፥ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፥ ጌታ ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፥ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።
በምልክትና በድንቅ ሥራ ኃይል፥ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል፥ ከኢየሩሳሌም ጀምሬ እስከ እልዋሪቆን ድረስ እየዞርሁ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ ሰብኬአለሁ።
ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ፥ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ ስለ እናንተ ስንል በእናንተ መካከል ምን ዓይነት ሰዎች እንደ ነበርን እናንተው ታውቃላችሁ።