መዝሙር 86:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፥ የክፉዎችም ማኅበር ነፍሴን ፈለጉአት፥ ላንተም ምንም ቦታ የላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ እብሪተኞች ተነሥተውብኛል፤ የግፈኞችም ጉባኤ ነፍሴን ይሿታል፤ አንተንም ከምንም አልቈጠሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤ አንተን የማይፈሩ ጨካኞች ሰዎች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ። |
አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።