መዝሙር 31:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔስ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፥ በድንጋጤ አልሁ፥ አንተ ግን ወደ አንተ በጮኽሁ ጊዜ የልመናዬን ቃል ሰማኸኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ቅዱሳኑ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ውደዱት! እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል፤ ትዕቢተኞችን ግን ፈጽሞ ይበቀላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ለእርሱ የተቀደሳችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን ውደዱት፤ እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል፤ ለትዕቢተኞች ግን ተገቢ ቅጣታቸውን ይሰጣል። |
ያገለግሉት ዘንድ የጌታንም ስም ለመውደድ አገልጋዮቹም ለመሆን ወደ ጌታ የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን፥ በቃል ኪዳኔኔም የሚጸኑትን ሁሉ፥
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ ጌታ አምላክህ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው? ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔርን እንድትፈራው፥ በመንገዱም ሁሉ እንድትሄድ፥ ጌታ አምላክህንም እንድትወደው፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ እንድታመልከው፥
ጌታ አምላክህን በመውደድ፥ በመንገዱም በመሄድና ትእዛዙን፥ ሥርዓቱንና ሕጉን በመጠበቅ ያዘዝሁን ካደርግክ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትበዛለህም፤ ጌታ አምላክም ትወርሳት ዘንድ በምትገባበት ምድር ይባርክሃል።
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።