እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፥ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጉጉት ሆንሁ።
ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤ በቤቴ ጕልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።
እንቅልፍ ከቶ በዐይኔ አይዞርም፤ በቤት ጣራ ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆኜአለሁ።
ለሙሴ መንገዱን አሳየ፥ ለእስራኤል ልጆችም ፈቃዱን።
ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ባልንጀራ ሆንሁ።
ማለዳን ከሚጠብቁ የሌሊት ጠባቂዎች ይልቅ፥ ነፍሴ ጌታን ትጠብቃለች፥ ማለዳን ከሚጠብቁ ጠባቂዎች ይልቅ።
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ለምን ራቅህ?
ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኃይሌም ተወችኝ፥ የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘ።
እግዚአብሔርን ሳስታውስ እተክዛለሁ፥ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች።