ምሳሌ 26:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በረዶ በበጋ ዝናብም በመከር እንደማይፈልግ ሁሉ፥ እንዲሁም ለሞኝ ክብር አይገባውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በረዶ በበጋ፣ ዝናብ በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ፣ ክብርም ለሞኝ አይገባውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በረዶ በበጋ ወራት፥ ዝናብም በመከር ወራት እንደማያስፈልግ ሁሉ ለሞኝ ክብር አይገባውም። |
ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።”
ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፥ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምጽን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ የሴኬም ነዋሪዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ፤