La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 10:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰፈሮቹንም ሁሉ ከኋላ ሆኖ የሚጠብቀው የዳን ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመጨረሻም የዳን ሰፈር ሰራዊት ለሁሉም ክፍሎች የኋላ ደጀን በመሆን በዐርማቸው ሥር ተጓዙ፤ አለቃቸውም የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሰፈሮቹ ሁሉ በኋላ የሆነ የዳን ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo



ዘኍል 10:25
12 Referencias Cruzadas  

ጌታ ቀድሟችሁ ያልፋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኮላ አትወጡም፤ በመኮብለልም አትሄዱም።


የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የጌታም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።


ከዳን የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር፥


በብንያምም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን አለቃ ነበረ።


በአሴርም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የኤክራን ልጅ ፋግኤል አለቃ ነበረ።


በአሥረኛውም ቀን የዳን ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር አቀረበ፤


ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በጌታ ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር፤ ተዋጊዎቹም በፊታቸው ይሄዱ ነበር፤ የኋላ ደጀንም የሆነው ሕዝብ ከጌታ ታቦት በኋላ ይመጡ ነበር፥ ካህናቱም እየሄዱ ቀንደ መለከቱን ይነፉ ነበር።


ተዋጊዎቹም ቀንደ መለከቱን በሚነፉ በካህናቱ ፊት ይሄዱ ነበር፥ የኋላ ደጀንም የሆነው ሕዝብ ከታቦቱ በኋላ ይሄድ ነበር፥ ካህናቱም እየሄዱ ቀንደ መለከቱን ይነፉ ነበር።