La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወስዶ በቤተ በመቅደሱ ጫፍ ላይ አቆመውና

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቀጥሎም ዲያብሎስ ኢየሱስን ወደ ቅድስት ከተማ በመውሰድ ከቤተ መቅደሱም ዐናት ላይ አውጥቶ፣

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ፥ ዲያብሎስ ኢየሱስን ወደ ቅድስት ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደስ ጣራ ጫፍ ላይ አቆመው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፦

Ver Capítulo



ማቴዎስ 4:5
11 Referencias Cruzadas  

በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሀያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።


የሕዝቡ መሪዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀረው ሕዝብ ከአሥሩ አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲቀመጡ ዕጣ ተጣጣሉ።


በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ።


በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፥ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ።


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።


ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስቷ ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።


ወደ ኢየሩሳሌም ደግሞ ወሰደው፤ በመቅደስም ጫፍ ላይ አቆመው፥ እንዲህም አለው፦ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ፥ ከዚህ ወደ ታች ራስህን ወርውር፤


ኢየሱስም መልሶ “ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ኀጢአቱ የባሰ ነው” አለው።


ከመቅደሱ ውጭ ያለውን አደባባይ ግን ተወው፤ አትለካውም፥ ምክንያቱም ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና፤ እነርሱም ለአርባ ሁለት ወር ያህል የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።