ማቴዎስ 11:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀንበሬ ልዝብ፥ ሸክሜም ቀላል ነውና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀንበሬ ልዝብ ነው፤ ሸክሜም ቀላል ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀንበሬ ልዝብ፤ ሸክሜም ቀሊል ነውና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። |
ሰው ሆይ፥ መልካም ምን እንደሆነ ለአንተ ነግሮሃል፤ ፍትሕን እንድታደርግ፥ ምሕረትን እንድትወድና ከአምላክህም ጋር በትሕትና እንድትሄድ ካልሆነ በቀር ጌታ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው?
በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፤”
ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።”