La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 10:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በምትገቡባት በማንኛዪቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የተገባው ሰው ማን እንደሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ አንድ ከተማ ወይም መንደር ስትገቡ ሊቀበላችሁ ፈቃደኛ የሆነ ሰው ፈልጋችሁ በቤቱ ዕረፉ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያው ቈዩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምትገቡበት ከተማ ወይም መንደር፥ ተገቢ የሆነ ሰው ማን እንደ ሆነ መርምሩ፤ ያንንም ስፍራ ለቃችሁ እስክትወጡ ድረስ ከእርሱ ጋር ቈዩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 10:11
14 Referencias Cruzadas  

እንግዳው ግን በሜዳ አያድርም ነበር፥ ደጄንም ለመንገደኛ እከፍት ነበር፥


ለመንገዳችሁ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።


ወደ ቤቱም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ፤


ወደ አንድ ቤት በምትገቡበት ጊዜ ከዚያች ከተማ እስክትወጡ ድረስ እዚያው ቆዩ፤


ሁሉም አይተው “ከኀጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ፤” ብለው አንጐራጐሩ።


በማናቸውም በምትገቡበት ቤት በዚያ ተቀመጡ፤ ከዚያም ካረፋችሁበት ቤት ወጥታችሁ ሂዱ።


እርሷም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፤” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።