ዘሌዋውያን 15:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ የሚፈስሰው ነገር ርኩስነቱ ይህ ነው፤ ፈሳሹ ነገር ከሰውነቱ ቢፈስስ ወይም ከመፍሰሱ ቢቆም፥ ለእርሱ ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰውነቱ የሚወጣው ፈሳሽ መፍሰሱን ቢቀጥል ወይም ባይቀጥል ሰውየው ርኩስ ነው፤ ፈሳሹም ርኩሰት የሚያስከትለው እንደዚህ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ማለት ከአባለ ዘሩ ቢፈስ ወይም መፍሰሱን ቢያቆም ያው ርኩስ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰውነቱ ፈሳሽ ለሚፈስሰው ሰው የርኵሰቱ ሕግ ይህ ነው፤ ፈሳሽ የሚፈስሰው ሰው ፈሳሹ እየፈሰሰው በሚኖርበት ጊዜ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ፈሳሹ ያረክሰዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለሚፈስሰው ነገር ርኩስነቱ ይህ ነው፤ ፈሳሹ ነገር ከሥጋው ቢፈስስ ወይም ከመፍሰሱ ቢቆም፥ ርኩስ መሆኑ ነው። |