መጽሐፈ ዮዲት 12:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልብስዋን ለመልበስና የሴቶች ጌጣጌጧን ሁሉ ለማድረግ ተነሣች፤ አገልጋይቷም ቀድማ ገባችና በየቀኑ ስትበላ አንጥፋ የምትቀመጥበትን ባጎስ የሰጣትን ምንጣፏን በሆሎፎርኒስ ፊት በምድር ላይ አነጠፈችላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥታም ልብሷን ለበሰች፤ የሴቶችንም ጌጥ ሁሉ ፈጽማ አጌጠች፤ ብላቴናዋም ከእርሷ ጋራ ሄደች፤ ከባግዋ የተቀበለችውን፥ በማደሪያዋ ያነጠፈላትን፥ ምሳም ስትበላ የምትቀመጥበትን ምንጣፏን በሆሎፎርኒስ ፊት በምድር ላይ አነጠፈችላት። |