መሳፍንት 8:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዜባሕና ጻልሙናንም፥ “በታቦር ላይ የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፥ “ሁሉም እንዲህ እንዳንተ ያሉ የንጉሥ ልጆች የሚመስሉ ናቸው” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛብሄልና ስልማናንም፣ “በታቦር ላይ የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ሁሉም እንዲህ እንደ አንተ ያሉ የንጉሥ ልጆች የሚመስሉ ናቸው” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጌዴዎን “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” ሲል ዜባሕንና ጻልሙናዕን ጠየቀ። እነርሱም “አንተን ይመስሉ ነበር፤ እያንዳንዳቸው የንጉሥ ልጅ ይመስላሉ” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛብሄልንና ስልማናን፥ “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “እንዳንተ ያሉ ነበሩ፤ አንተንም ይመስሉ ነበር፤ መልካቸውም እንደ ነገሥት ልጆች መልክ ነበረ” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛብሄልና ስልማናን፦ በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ? አላቸው። እነርሱም፦ እንደ አንተ ያሉ ነበሩ፥ አንተንም ይመስሉ ነበር፥ መልካቸውም እንደ ንጉሥ ልጆች መልክ ነበረ ብለው መለሱለት። |
በወገባቸው ዝናር የታጠቁ፥ በራሳቸውም ላይ መጠምጠሚያ ያንጠለጠሉ፥ ሁሉም የተወለዱባት አገር የከለዳ የሆነች የባቢሎን ልጆች የሆኑትን ባለሥልጣኖችን ይመስሉ ነበር።
ዲቦራ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባራቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺህ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤
ጌዴዎንም፥ “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ናቸው፤ ባትገድሏቸው ኖሮ እኔም እንደማልገድላችሁ በሕያው ጌታ ስም አረጋግጥላችሁ ነበር” ብሎ መለሰላቸው።
የሱኮትንም ሰዎች፥ “የምድያምን ነገሥታት ዜባሕንና ጻልሙናን በማሳደድ ላይ ስለ ሆንኩ የተከተሉኝም ሰዎች ስለ ደከሙ ብኝ እባካችሁ የሚበሉትን እንጀራ ስጧቸው” አላቸው።