ባያትም ጊዜ ልብሱን በመቅደድ፥ “ወይኔ ልጄ ጉድ አደረግሽኝ ጭንቅም ላይ ጣልሺኝ፤ ማስቀረት የማልችለውን ስእለት ለጌታ ተስያለሁና” ብሎ በኀዘን ጮኸ።
መሳፍንት 21:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ልጁን ለብንያማዊ የሚድር ርጉም ይሁን’ ብለን እኛ እስራኤላውያን ስለ ተማማልን እንግዲህ ልጆቻችንን ልንድርላቸው አንችልም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ልጁን ለብንያማዊ የሚድር ርጉም ይሁን’ ብለን እኛ እስራኤላውያን ስለ ተማማልን እንግዲህ ልጆቻችንን ልንድርላቸው አንችልም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ከእኛ መካከል ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብንያማዊ ቢድር የተረገመ እንደሚሆን በመሐላ ቃል የገባን ስለ ሆነ ሴቶች ልጆቻችንን ያገቡ ዘንድ ልንፈቅድላቸው አንችልም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች፥ “ልጁን ለብንያም የሚሰጥ ርጉም ይሁን ብለው ምለዋልና እኛ ከልጆቻችን ሚስቶችን ለእነርሱ መስጠት አንችልም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች፦ ልጁን ለብንያም የሚድር ርጉም ይሁን ብለው ምለዋልና እኛ ልጆቻችንን ለእነርሱ ማጋባት አይሆንልንም አሉ። |
ባያትም ጊዜ ልብሱን በመቅደድ፥ “ወይኔ ልጄ ጉድ አደረግሽኝ ጭንቅም ላይ ጣልሺኝ፤ ማስቀረት የማልችለውን ስእለት ለጌታ ተስያለሁና” ብሎ በኀዘን ጮኸ።
አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ቢቃወሙ፥ ‘በጦርነት ጊዜ ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶች ስላላገኘን ነውና እነርሱን በመርዳት ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም ደግሞ ልጆቻችሁን ፈቅዳችሁ ያልዳራችሁ በመሆናችሁ በደለኞች አትሆኑም’ እንላቸዋለን።”