መሳፍንት 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጥሎም፥ “በል ና፤ ወደ ጊብዓ ወይም ወደ ራማ ለመድረስ እንሞክርና ከዚያ በአንዱ ስፍራ እናድራለን” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም፣ “በል ና፤ ወደ ጊብዓ ወይም ወደ ራማ ለመድረስ እንሞክርና ከዚያ በአንዱ ስፍራ እናድራለን” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሽከሩንም “ና ከእነዚህ ቦታዎች ወደ አንዱ እንቅረብ፤ በጊብዓ ወይም በራማ እንደር” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውንም፥ “ና፤ ከእነዚህ ስፍራ ወደ አንዱ እንቅረብ፤ በገባዖን ወይም በራማ እንደር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሽከሩንም፦ ና፥ ከእነዚህ ስፍራ ወደ አንዱ እንቅረብ፥ በጊብዓ ወይም በራማ እንደር አለው። |
በጊብዓ ቀንደ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ “ብንያም ሆይ! ከአንተ ጋር ነን እያላችሁ በቤትአዌን ላይ የማስጠንቀቂያውን ነጋሪት ድምፅ አሰሙ።”
ጼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባል ኢያቡስ፥ ጊብዓና ቂርያትይዓሪም፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።