መሳፍንት 16:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደሊላም አዳዲስ ገመዶች ወስዳ አሰረችው፤ ሰዎች በጓዳ ውስጥ ተደብቀው ነበር፤ እርሷም፥ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። እርሱ ግን ክንዱ የታሰረባቸውን ገመዶች እንደ ፈትል ክር በጣጠሳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደሊላም አዳዲስ ገመዶች ወስዳ አሰረችው፤ ሰዎች በጓዳ ውስጥ ተደብቀው ነበር፤ እርሷም፣ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። እርሱ ግን ክንዱ የታሰረባቸውን ገመዶች እንደ ፈትል ክር በጣጠሳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደሊላም አዲስ ገመድ ወስዳ አሰረችው፤ በሌላ ክፍል ሆነው የሚጠባበቁ ወንዶች ስለ ነበሩ እርሷ “ሶምሶን፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” ስትል ጮኸች፤ እርሱ ግን ገመዱን ከክንዱ እንደ ፈትል በጣጠሰው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደሊላም ሰባት አዳዲስ ገመዶች ወስዳ በእነርሱ አሰረችው፤ የሚያደቡትም ሰዎች በጓዳዋ ውስጥ ተቀምጠው ነበር። እርስዋም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ገመዶችንም ከክንዱ እንደ ፈትል በጣጠሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደሊላም አዲስ ገመድ ወስዳ በእርሱ አሰረችው፥ በጓዳዋም የተደበቁ ሰዎች ተቀምጠው ነበር። እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ገመዱንም ከክንዱ እንደ ፈትል በጣጠሰው። |
ሳምሶን ሌሒ እንደደረሰም ፍልስጥኤማውያን እየጮኹ ወደ እርሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት። እጆቹ የታሰሩበትም ገመድ እሳት ውስጥ እንደ ገባ የተልባ እግር ፈትል ሆኖ ከእጆቹ ላይ ወደቀ።
ደግሞም ደሊላ ሳምሶንን፥ “እስካሁን አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል። እባክህን አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ” አለችው። እርሱም መልሶ፥ “የራስ ጠጉሬን ሰባት ቈንዳላዎች ከድር ጋር ጐንጉነሽ በችካል ብትቸክይው፥ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።