መሳፍንት 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሰዎች በኰረብታማው አገር፥ በኔጌብና በቈላማው አገር የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ወረዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሰዎች በኰረብታማው አገር፣ በኔጌብና በምዕራቡ ኰረብታ ግርጌ የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ወረዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሰዎች በተራራማው አገር፥ በኔጌብና በቈላማው አገር የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ዘመቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ የይሁዳ ልጆች በተራራማው ሀገርና በደቡብ በኩል በቈላው ውስጥ የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ሊወጉ ወረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ የይሁዳ ልጆች በተራራማው አገርና በደቡብ በኩል በቈላውም ውስጥ የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ሊወጉ ወረዱ። |
በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው።
በተራራማው አገር፥ በቈላውም፥ በዓረባም፥ በቁልቁለቱም፥ በምድረ በዳውም፥ በደቡቡም ያሉ ኬጢያውያን አሞራውያንም ከነዓናውያንም ፌርዛውያንም ኤዊያውያንም ኢያቡሳውያንም ዘንድ ነበር።
የይሁዳ ሰዎች በኬብሮን በሚኖሩ ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ኬብሮን ቀደም ሲል ቂርያት-አርባዕ ተብላ ትጠራ ነበር፤ እነርሱም ሼሻይን፥ አሒማንንና ታልማይኖችን ድል አደረጉ።