መሳፍንት 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ተነሥተው በዳቤር በሚኖሩት ሰዎች ላይ ዘመቱ፤ የዳቤር የቀድሞ ስም ቂርያት ሴፌር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ቀደም ሲል ቂርያትሤፍር ተብላ በምትጠራው በዳቤር በሚኖሩት ሰዎች ላይ ዘመቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም የይሁዳ ሰዎች በደቢር ኗሪዎች ላይ ዘመቱ፤ በዚያን ጊዜ ከተማይቱ “ቂርያት ሴፌር” ተብላ ትጠራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወደ ዳቤር ሰዎች ሄዱ፤ አስቀድሞም የዳቤር ስም ሀገረ መጻሕፍት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም የዳቤርን ሰዎች ሊወጋ ሄደ፥ አስቀድሞም የዳቤር ስም ቅርያትሤፍር ነበረ። |