ኢዩኤል 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ስደዱ፥ መጥመቂያውም ሞልቶአልና ኑ እርገጡ፥ ክፉታቸውም በዝቶአልና መጥመቂያ ሁሉ ፈርሶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማጭዱን ስደዱ፤ መከሩ ደርሷልና፤ ኑ ወይኑን ርገጡ፤ የወይን መጭመቂያው ሞልቶ፣ ከጕድጓዶቹም ተርፎ ፈስሷልና፤ ክፋታቸው እንደዚህ ታላቅ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱ ክፋት እጅግ በዝቶአል፤ የደረሰ መከር በማጭድ እንደሚታጨድ እጨዱአቸው፤ የወይን ዘለላ በመጥመቂያው ሞልቶ እንደሚረገጥ ርገጡአቸው፤” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭመቂያውም ሞልቶአልና ኑ ርገጡ፤ ክፋታቸውም በዝቶአልና መጭመቂያ ሁሉ ፈስሶአል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ስደዱ፥ መጥመቂያውም ሞልቶአልና ኑ እርገጡ፥ ክፉታቸውም በዝቶአልና መጥመቂያ ሁሉ ፈርሶአል። |
“መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”
ሳምኬት። ጌታ ኃያላኖቼን ሁሉ ከውስጤ አስወገዳቸው፥ ጐልማሶቼን ያደቅቅ ዘንድ ጉባኤን ጠራብኝ፥ ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በመጥመቂያ እንደሚረገጥ አድርጎ ረገጣት።
ከዚያም አየሁ፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰው ልጅን የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው።
አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።