ኢዮብ 37:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ የደመናውን መንሳፈፍ፥ ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናት ሚዛን ጠብቀው እንዴት እንደሚንሳፈፉ፣ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን፣ የርሱን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመናን በሕዋው ላይ የሚያንሳፍፈውንና ሁሉን የሚያውቀውን የአምላክን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የደመናትን ክፍሎች፥ አስፈሪ የሆነውንም የኀጢአተኞችን አወዳደቅ ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ የደመናውን ሚዛን፥ ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን? |
እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥