ኢዮብ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ እንዲሁም፦ ‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፤ ‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ያች የተወለድሁባት ቀን ትጥፋ፥ ያችም፦ ወንድ ልጅ ነው ያሉባት ሌሊት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ ያም፦ ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ሌሊት። |
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።