ኢዮብ 24:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፥ በብርድ ጊዜ የሚደረብ የላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፤ በብርድም ጊዜ የሚለብሱት የላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሊቱን ሙሉ ራቁታቸውን ተኝተው ያድራሉ፤ ብርድ የሚከላከሉበትም ልብስ የላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙዎችን የተራቈቱትንም ያለ ልብስ ያሳድሩአቸዋል። መጐናጸፊያቸውንም ይገፍፏቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፥ በብርድ ጊዜ መጐናጸፊያ የላቸውም። |
እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።