የወራታቸውስ ቍጥር ከተቈረጠ፥ ከእነርሱ በኋላ የቤታቸው ደስታ ምን ይሆናቸዋል?
ሰው ወራቱ በተገባደደ ጊዜ፣ ለቀሪ ቤተ ሰቡ ምን ይገድደዋል?
ሰው ከሞተ በኋላ፥ ስለ ልጆቹ ምን ደንታ ይኖረዋል?
የወደደውን በቤቱ ውስጥ ያደርጋል። ወራቶቹም ከቍጥር ድንገት ይጐድላሉ።
የወራታቸውስ ቍጥር ቢቈረጥ፥ ከእነርሱ በኋላ የቤታቸው ደስታ ምን ይሆናቸዋል?
ልጆቹ ቢከብሩ አያውቅም፥ ቢዋረዱም አያይም።
የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥ እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት።
ዐይኖቻቸው ጥፋታቸውን ይዩ፥ ሁሉን ከሚችል አምላክ ቁጣ ይጠጡ።
ከፍ ከፍ ባሉት ላይ ለሚፈርደው እግዚአብሔር ሰው እውቀትን ሊያስተም ይችላልን?
በመንገዴ ጉልበቴ ዛለ፦ ዘመኔም አጠረ።
ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፥ ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።