ኢዮብ 15:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኑ ሳይደርስ ጊዜው ይፈጸማል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጊዜው ሳይደርስ ይጠወልጋል፤ ቅርንጫፉም አይለመልምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጊዜው ሳይደርስ ግንዱ እንደሚደርቅና ቅርንጫፎቹም እንደማይለመልሙ ዛፍ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀኑ ሳይደርስ መከሩ ይጠፋል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀኑ ሳይደርስ ጊዜው ይፈጸማል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም። |
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።