እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኢዮብ 12:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም ለምድር ተናገር፥ እርሷም ታስተምርሃለች፥ የባሕርም ዓሣዎች ይነግሩሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለምድር ተናገሩ፤ ታስተምራችኋለች፤ የባሕርም ዓሣ ይነግራችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም ለምድር ተናገር፤ እርስዋም ታስተምርሃለች፤ የባሕርም ዓሣዎች ይነግሩሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምድር ንገራት፥ እርስዋም ትተረጕምልሃለች፤ የባሕርም ዓሣዎች ያስረዱሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ለምድር ተናገር፥ እርስዋም ታስተምርሃለች፥ የባሕርም ዓሣዎች ይነግሩሃል። |
እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።