ይህ ሁሉ ራእይ እንደ ታተመ የመጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው ባዘዙት ጊዜ እርሱ፦ “ታሽጓልና አልችልም” ይላቸዋል፤
ኢሳይያስ 29:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ “ማንበብ አላውቅም” ይላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ጥቅልሉን መጽሐፍ ማንበብ ለማይችል ሰው፣ “እባክህን አንብብልን” ብላችሁ ብትሰጡ፣ “ማንበብ አልችልም” ይላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንበብ ወደማይችል ሰው ወስዳችሁ “አንብብልን” ብትሉት፥ “እኔ ማንበብ አልችልም” ይላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፥ “ይህን አንብብ” ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፥ “ማንበብ አላውቅም” ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፦ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ ማንበብ አላውቅም ይላቸዋል። |
ይህ ሁሉ ራእይ እንደ ታተመ የመጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው ባዘዙት ጊዜ እርሱ፦ “ታሽጓልና አልችልም” ይላቸዋል፤
ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛል።
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።