ኢሳይያስ 25:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ተራራ ላይ፣ በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣ በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ተራራ ላይ ሕዝቦችን ሁሉ ጋርዶ የነበረውን የሐዘን መጋረጃ ያስወግዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ተራራ ላይ ይህን ሁሉ ለአሕዛብ ሰጠ፤ ምክሩ ለአሕዛብ ሁሉ ናትና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፥ በአህዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል። |
ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ለመታየት ወደ እርሷ ወደ ሰማይ ገባ።