ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
ዕብራውያን 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉድለት አግኝቶባቸዋልና እንዲህ ይላቸዋል፦ “እነሆ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምመሠርትበት ወራት ይመጣል፥ ይላል ጌታ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ጕድለት በማግኘቱ እንዲህ ይላቸዋል፤ “ከእስራኤል ቤትና፣ ከይሁዳ ቤት ጋራ፣ አዲስ ኪዳን የምገባበት፣ ጊዜ ይመጣል፤ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ነቀፋ መኖሩን በማመልከት እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ከእስራኤል ሕዝብና ከይሁዳ ሕዝብ ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እነርሱን ነቅፎ እንዲህ አለ፥ “እነሆ፥ ለቤተ እስራኤልና ለቤተ ይሁዳም አዲስ ኪዳን የምሠራበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱን እየነቀፈ ይላቸዋልና፦ እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል ጌታ፤ |
ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
“ስለዚህ፥ እነሆ፦ ‘የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ብለው ዳግመኛ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፤
እነሆ፥ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስበት ዘመን ይመጣልና፥ ይላል ጌታ፤ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ይወርሱአታል፥ ይላል ጌታ።”
ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።
የሰላም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል፤ አጸናቸዋለሁ፥ አበዛቸዋለሁ፥ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘለዓለም አኖራለሁ።
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሰረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።
እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ላልሆነ፥ ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን አበቃን፤ ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
አሁን ግን በተሻለ ተስፋ ቃል ስለ ተመሠረተ፥ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን የተሻለ እንደሆነ ሁሉ፥ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፥፥
በዚህ ምክንያት የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞቱ ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘለዓምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።