ዘፍጥረት 42:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፥ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ከሄዱት ሰዎች መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፣ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ከሄዱት ሰዎች መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከነዓን ምድርም ራብ ገብቶ ስለ ነበር የያዕቆብ ልጆች ከሌሎች ሰዎች ጋር እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡት ጋር ገቡ፤ በከነዓን ሀገር ራብ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ በከነዓን አገር ራብ ነበረና። |
በዳዊት ዘመነ መንግሥት፥ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት ጌታን ጠየቀ፤ ጌታም፥ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፥ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።
ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።