ሕዝቅኤል 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውኃም በልክ ትጠጣለህ፥ የኢን መስፈሪያ አንድ ስድስተኛ ትጠጣለህ፥ በየጊዜውም ትጠጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትጠጣውንም ውሃ አንድ ስድስተኛ ሂን ለክተህ አስቀምጥ፤ በተወሰነ ጊዜ ትጠጣዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትጠጣውም ውሃ የተመጠነ መሆን ስለሚገባው በቀን ሁለት ኩባያ ብቻ ትጠጣለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃውንም በልክ የኢን መስፈሪያ ከስድስት እጅ አንድ እጅ ትጠጣለህ፤ በየጊዜው ትጠጣዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውኃውንም በልክ የኢን መስፈሪያ ከስድስት እጅ አንድን እጅ ትጠጣለህ፥ በየጊዜው ትጠጣዋለህ። |
ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ እኔ በኢየሩሳሌም የምግብን በትር እሰብራለሁ፥ ምግብ እየፈሩ በሚዛን ይበላሉ፥ ውኃም እየደነገጡ በልክ ይጠጣሉ፤