ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ በታላቅ በደል ነበርን፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስለ ኃጢአታችን እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናቶቻችን ለሰይፍ፥ ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለእፍረት በምድር ነገሥታት እጅ ተሰጠን።
ሕዝቅኤል 23:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በዝሙት ላረጀችው፦ አሁን ከእርሷ ጋር ያመነዝራሉ፥ እርሷም ታመነዝራለች አልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም በአመንዝራነት ሰውነቷ ስላለቀው፣ ‘እርሷ ሕይወቷ ይኸው ስለ ሆነ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ይጠቀሙባት’ አልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም በልቤ ‘እነዚህ ወንዶች ዝሙት የሚፈጽሙት በአመንዝራነት ሰውነትዋ ካለቀ ሴት ጋር ነው’ አልኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፦ ‘አሁን ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ፤ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ታመነዝራለች፤’ አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም በምንዝር ላረጀችው፦ አሁን ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ታመነዝራለች አልሁ። |
ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ በታላቅ በደል ነበርን፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስለ ኃጢአታችን እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናቶቻችን ለሰይፍ፥ ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለእፍረት በምድር ነገሥታት እጅ ተሰጠን።